ኢትዮጵያ ቡና የሁለት አጥቂዎችን ዝውውር ይፋ አደረገ

ኢትዮጵያ ቡና ከቤኒን እና ቶጎ ሁለት አጥቂዎችን ማስፈረሙን በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል፡፡ ቡና ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ቶጎዊው አደም ሆሶሮቪ በጋና ለኸርትስ ኦፍ ላየንስ ፣ አቢኪዮ ቻኪሩ ለኦማኑ ሙስካት ክለብ የተጫወቱ ሲሆን 7 እና 13 ቁጥር ማልያ እንደሚለብሱም ተገልጧል፡፡

ሙሉ ዘገባው ይህንን ይመስላል፡-

[[

በ2006 ዓ.ም በፕሪምየር ሊጉ እና ሌሎች ውድድሮች የነበረው የኢትዮጵያ ቡና መሰረታዊ ችግር የአጥቂ ክፍሉ በሚጠበቀው ደረጃ ጎሎች አለማስቆጠሩ ነው ፡፡ ይህንን ክፍተት ለመድፈን ከሀገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ ተጫዋቾችን በማየት ሂደት ላይ የከረመው ክለቡ ሁነኛ አጥቂዎችን ከውጪ የማስፈረም ሂደቱን ጨርሷል ፡፡

በዚህ መሰረትም የተለያዩ የአፍሪካ አጥቂዎችን ቪድዮ እና ሌሎች መረጃዎች ሲያጣራ ቆይቶ በግብዣ ደብዳቤ ሁለት አጥቂዎችን ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ከቡድኑ ጋር ሀዋሳ ለሙከራ ሲያያቸው ቆይቷል ፡፡

ለጋናው ኸርተስ ኦፍ ላይን ይጫወት የነበረውን እና የቶጎ ዜግነት ያለው ኤደም ሆሶሮቪ ኮዶዞ ለሃገሩ ብሄራዊ ቡድኑ ካገለገለው በተጨማሪ በተለያዩ ክለቦች ኮከብ ግብ አግቢ የሆነ እንዲሁም በጋናው ክለብ ኸርትስ ኦፍ ላይን ቆይታውም ከ21 በላይ ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ የፊት መስመር አጥቂ ነው ፡፡

ለኦማኑ ሙስካት ክለብ በተመሳሳይ በአጥቂ መስመር የሚጫወተው ቤኒናዊ አቢኪዮ ቻኪሩ አላድም በብሄራዊ ቡድኑ እና በተጫወተባቸው ክለቦች ሁነኛ ግብ አዳኝ ነው ፡፡ ሁለቱ አጥቂዎች ለቡና ለመጫወት ሂደቶችን አጠናቀው ዛሬ ከሰዓት ለቡና የፈረሙ ሲሆን በቀጣይ በምርጫቸው 7 እና 13 ቁጥር ማሊያ ለብሰው የቡናን የፊት መስመር ይመራሉ ፡፡

]]


ፎቶ – የኢትዮጵያ ቡና ፌስቡክ ገፅ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *