ሀዋሳ ከተማ 3-0 ወልዋሎ | የአሰልጣኞች አስተያየት

ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታዎች መካከል ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ ወልዋሎን አስተናግዶ 3-0 ከረታበት ጨዋታ ፍፃሜ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

” የመስመር ላይ አጨዋወታችን የተሻለ ነበር ” አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ – ሀዋሳ ከተማ

ስለ ጨዋታው

“ጨዋታው ለኔ እንደ ጅማሮው ጥሩ ነው። በተለይ  የመስመር ላይ አጨዋወታችን የተሻለ ነበር። ይህ ነገር ይቀጥላል የሚል እምነትም አለኝ። አንድ የመስመር ተከላካይ አምጥተናል፤ ይህንን ክፍል ይበልጥ ያሰፋልናል ብዬ አስባለሁ፡፡ በአጠቃላይ በድሉ ተደስቻለሁ።

ስለ አዳነ ግርማ የመሀል ሜዳ እንቅስቃሴ…

“አዳነ ትልቅ ልምድ ያለው ተጫዋች ነው። እሱ በዛ ቦታ ላይ መኖሩ ቡድኑን በመምራት በማስተባበር አስተዋጽኦው የጎላ ነበር። የመጣበት አንዱ ምክንያትም ይሄ ነበር።

በቀጣይ ተጠናክሮ ስለመቅረብ…

“ለአንድ ቡድን ስነ-ልቡና አስፈላጊ ነገር ነው። ያንን ከገነባህ የአሸናፊነት መንፈስህ ጠንካራ ይሆናል። በዚህ ቡድን ከዚህ በፊት የሌለው ህብረቱ ይመስለኛል፤ አሁን ላይ ህብረቱ ጥሩ ነው። የማሸነፍ ስሜትን ማስቀጠል አለብን፤ ከሜዳ ውጭ ያለንን ታሪክም ለመቀየር እንሰራለን።

” ሀዋሳዎች ማሸነፍ ይገባቸዋል። ” የወልዋሎ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም

ስለ ጨዋታው…

” ጎል እስኪቆጠርብን ደቂቃ ድረስ ለመቋቋም ሞክረናል። በመጨረሻ የእረፍት ሰአት ከተቆጠረብን ግብ በኃላ ግን ብልጫ ተወስዶብናል። ለኔ ጨዋታው ጥሩ ነበር፤ በሁለተኛው አጋማሽ ግን በሀዋሳ ብልጫ ተወስዶብናል። የጥንቃቄ እና የትኩረት ማጣት ችግሮች ነበሩብን። ሀዋሳዎች እንዳሳዩት ብልጫ ውጤቱ ይገባቸዋል። እኛም በፀጋ ተቀብለናል፤ እንኳን ደስ ያላችሁም ለማለት እወዳለሁ”

በቀጣይ…

“አሁን ላይ ቡድኔን እንደ አዲስ ነው የገነባሁት። በጊዜ ሂደት እናስተካክለዋለን፤ በተለይ በሜዳችን በደጋፊዎቻችን ፊትም ስለምንጫወት የተሻለ የማሸነፍ ስሜትን እየፈጠርን እንመጣለን። ዛሬ ሜዳው አርቴፊሻል መሆኑ የፈጠረው ተፅእኖ አንዳለ ሆኖ በቀጣይ ስህተቶቻችንን አርመን ለመቅረብ እንዘጋጃለን”


ማስታወቂያ
የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የዋናው እግርኳስ ቡድን የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች የቪድዮ ቀረጻ እና የጨዋታ ትንተና የሚያደርግ ባለሙያ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ሙያ ላይ የተሰማሩ አካላት በስራው ላይ ያላቸውን የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ በመያዝ ሜክሲኮ በሚገኘው የክለቡ ጽህፈት ቤት በአካል በመቅረብ የፍላጎት ማሳወቂያ እና የመወዳደርያ ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ – 0115-534949 ; 0115-532051

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ