ካሜሩን 2019| በዓምላክ እና ኢትዮጵያውያን ረዳቶቹ ወደ ማዳጋስካር ያመራሉ

ትላንት የቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜን የመራው በዓምላክ ተሰማ እና ኢትዮጵያዊያን ረዳቶቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ 5ኛ የምድብ ጨዋታን በዳኝነት ይመራሉ።

በምድብ ሀ በታሪኳ ለመጀመርያ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ያረጋገጠችው የአህጉሪቱ ትልቋ ደሴት ማዳጋስካር እና መውደቋን አስቀድማ ያረጋገጠችው ሱዳን ኅዳር 9 አንታናናሪቮ በሚገኘው ሲናፕስ ስታድየም የሚያደርጉት ጨዋታ በበዓምላክ ተሰማ ዋና ዳኝነት ይመራል። በትላንትናው ዕለት የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜን በብቃት የመራው በዓምላክ በማጣርያ ውድድሮች ለአራተኛ ጊዜ በዋና ዳኝነት የሚመራ ሲሆን ተመስገን ሳሙኤልም ለአራተኛ ጊዜ አብሮት በረዳት ዳኝነት የሚዳኝ ይሆናል። ትግል ግዛው ሌላው ረዳት ዳኛ ሲሆን በላይ ታደሰ ደግሞ በአራተኛ ዳኛነት ተመድቧል።

በዓምላክ በምድብ ሀ የማጣርያ ጨዋታ ሲመራ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ሴኔጋል ከ ሱዳን ያደረጉት ሶስተኛ የምድብ ጨዋታ መምራቱ ይታወሳል።

ከዳኞች ጋር በተያያዘ ዜና ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ላይ ጋናን የምታስተናግድበት ጨዋታን ደቡብ አፍሪካዊያኑ ቪክቶር ጎሜዝ (ዋና)፣ ዛኬሌ ቱሲ (ረዳት) እና ሴሎ ሞሺዲ (ረዳት) የሚመሩት ይሆናል።

ተዛማጅ ፅሁፍ | ኢትዮጵያውያን ዳኞች የኦሊምፒክ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታን ይመራሉ