ወንድማማቾቹ በአውስራሊያ….

በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የሚጫወቱ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ ለዛሬ በአውስትራልያ የሚጫወቱ ወንድማማቾችን እናስተዋውቃችኋለን፡፡

ቴድሮስ ያቢዮ

ቴዲ ያቢዮ

ሙሉ ስሙ ቴድሮስ ያቢዮ ይባላል፡፡ በአውስትራሊያ ናሽናል ፕሪሚየር ሊግ ለሚወዳደረው አልባን ሴይንትስ የሚጫወት ትውልደ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ነው፡፡

ዲሴምበር 14 ቀን 1992 የተወለደው ሰለሞን ከዚህ ቀደም ለሜልቦርን ቪክትሪ የተጫወተ ሲሆን በአጥቂ ስፍራ የሚጫወት የ22 አመት ወጣት ነው፡፡

ሰለሞን ያቢዮ

ሰለሞን ያቢዮ

ኦክቶበር 26 ቀን 1996 የተወለደው ሰለሞን የቴድሮስ ታናሽ ወንድም ሲሆን እንደ ወንድሙ ሁሉ በአውስትራሊያ ናሽናል ፕሪሚየር ሊግ ለሚወዳደረው አልብን ሴይንትስ የሚጫወት የ18 አመት ታዳጊ ነው፡፡

በመስመር አማካይነት ፣ በአጥቂ አማካይነት እና አጥቂነት መጫወት የሚችለው ሰለሞን ባለፈው አመት ለኢትዮጵያ ወጣት እና ታዳጊ ቡድን ለመጫወት ፍላጎት አሳይቶ ነበር፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያዊው የቀድሞ የሆላንድ ወጣት ቡድን ተጫዋች የሱፍ ሄርሲ በአውስትራልያ ሊግ የሚጫወት ሌላው ትውደ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ነው፡፡

የሱፍ ሄርሲ እና ቴድሮስ ያቢዮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *