ኢትዮጵያውያን ዳኞች ሁለት የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን ይመራሉ

የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የ2018/19 የውድድር ዘመን በመጪው ሳምንት አጋማሽ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ዳኞችም በቅድመ ማጣርያው ሁለት ጨዋታ ላይ በዳኝነት እንዲመሩ በካፍ ተጠርተዋል፡፡

ኅዳር 18 የሚደረገው የሊቢያው ኤል ናስር እና የደቡብ ሱዳኑ አል-ሒላል ጁባ ጨዋታን እንዲመራ የተመረጠው ለሚ ንጉሴ ሲሆን ትግል ግዛው እና በላቸው ይታየው ረዳቶቹ ናቸው፡፡ በላይ ታደሰ ደግሞ በአራተኛ ዳኝነት ተመድቧል፡፡

የቻምፒየንስ ሊጉ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሲቀጥል በዚምባበዌው ፕላቲንየም እና በማዳጋስካሩ ሲናፕስ መካከል የሚደረገውን ጨዋታም በተመሳሳይ በለሚ ንጉሴ ይመራል፡፡ ተመስገን ሳሙኤል እና ትግል ግዛው ረዳቶቹ ናቸው፡፡ በዓምላክ ተሰማ ደግሞ በአራተኛ ዳኝነት አብሮ የሚጓዝ ይሆናል፡፡

በአዲስ አካሄድ ከሙሉ ዓመት ካላንደር ይልቅ ከኦገስት እስከ ሜይ በሚደረግ ውድድር የሚከናወነው የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ላይ ተሳታፊ የሆኑት ጅማ አባ ጅፋር ከጅቡቲው ቴሌኮም (ቻምፒየንስ ሊግ) እና መከላከያ ከናይጄርያው ሬንጀርስ (ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ) ጋር የሚጫወቱ ይሆናል፡፡


የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች | LINK

ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታዎች | LINK