ቻምፒየንስ ሊግ | ጅማ አባጅፋርን የሚገጥመው የአል አህሊ የነገ ቡድን ዝርዝር

የግብፁ ድረ ገፅ ኪንግ ፉት ጅማ አባ ጅፋርን የሚገጥመውን አል አህሊ ሙሉ ስብስብ ይፋ አድርጓል።

በ2019 የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ውስጥ ለመካተት የኢትዮጵያው ጅማ አባ ጅፋር ነገ በአሌክሳንድሪያ አል አህሊን እንደሚገጥም ይጠበቃል። በጨዋታው ባለሜዳዎቹ አል አህሊዎች የሚጠቀሙትን ቡድን የተጫዋቾች ዝርዝር በሀገሪቷ መቀመጫውን ያደረገው የእግር ኳስ ድረ ገፅ ኪንግ ፉት አስነብቧል።

እንደ ድረ ገፁ ዘገባ ከሆነ በጉዳት እየታመሰ የሚገኘው የአል አህሊ የኋላ መስመር ለነገው ጨዋታ ሦስት ተጫዋቾችን ብቻ ለማካተት ተገዷል። በዚህም ምክንያት የቀኝ መስመር ተከላካዩ መሀመድ ሀኒ ከሳሊፍ ኩሊባሊ ጋር በመሀል ተከላካይነት እንደሚጣመሩ ሲጠበቅ አይማን አሽረፍ በግራ ፤ አማካዩ ከሪም ናድቬድ ደግሞ በቀኝ መስመር ተከላካይነት እንደሚሰለፉ ይገመታል።

በሌላ በኩል የቡድኑ አምበል ሆሳም አሻወር ወደ ቡድኑ ስብስብ የተመለሰ ሲሆን ዋሊድ አዛሮ ፣ ሳላ ሞሀሰን ፣ አህመድ ፋቲ ፣ መሀመድ ኤል ሻናዊ እና አሊ ማኑን በጉዳት ጅማ አባ ጅፋርን በሚገጥመው ቡድን ውስጥ አልተካተቱም።

ሙሉ ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች፡ አሊ ሎትፊ ፣ ሸሪፍ ኢክራሚ

ተከላካዮች፡ ሳሊፍ ኩሊባሊ ፣ አይማን አሽረፍ ፣ መሐመድ ሀኒ

አማካዮች፡ ሆሳም አሻወር ፣ ሔሻም መሀመድ ፣ ከሪም ናድቬድ ፣ ሚዶ ጋባር ፣ አመር ኤል ሱሊያ ፣ ኢስላም ሞሀርብ ፣ ዋሊድ ሱለይማን ፣ ናስት ማሀር ፣ መሀመድ ሸሪፍ ፣ አህመድ ሀሞውዲ

አጥቂ፡ ማርዋን ሞህሰን

በተያያዘ አል አህሊን ለመግጠም ወደ አሌክሳንድሪያ በጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሚጓዘው የጅማ አባ ጅፋር 18 ተጫዋቾች ስብስብ ይህንን ይመስላል:-

ግብ ጠባቂዎች፡ ዳንኤል አጄይ፣ ዘሪሁን ታደለ

ተከላካዮች፡ አዳማ ሲሶኮ ፣ ኤልያስ አታሮ ፣ ተስፍዬ መላኩ ፣ ያሬድ ዘውድነህ ፣ ከድር ኸይረዲን፣ ዐወት ገ/ሚካኤል

አማካዮች፡ አክሊሉ ዋለልኝ ፣ መስዑድ መሐመድ ፣ ኤልያስ ማሞ ፣ ይሁን እንደሻው ፣ ኄኖክ ገምቴሳ ኤርሚያስ ኃይሉ ፣ አስቻለው ግርማ

አጥቂዎች፡ ዲዲዬ ለብሪ ፣ ሴዲቤ ማማዱ ፣ ቢስማርክ አፒያ