ሸመልስ በቀለ ወደ ምስር  አል ማቃሳ ተዛዋውሯል

ከፔትሮጀክት ጋር ስኬታማ ሶስት ዓመታቶችን ያሳለፈው ኢትዮጵያዊው አማካይ ሽመልስ በቀለ ወደ ሌላኛው የግብፅ ክለብ ምስር  አል ማቃሳ በሶስት አመት  የውል ስምምነት ተቀላቅሏል፡፡

በሀዋሳ ከተማ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረውና ቀጥሎም በቅዱስ ጊዮርጊስ  መጫወት የቻለው  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሽመልስ በቀለ ከኢትዮጵያ ውጭ በመውጣት በሊቢያው ክለብ አል አህሊ ትሪፖሊ ካመራ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ወደ ሱዳን አምርቶ ለኤልሜሪክ ተሰልፎ ተጫውቷል። ቀጥሎ ወደ ግብፅ በማቅናት ያለፉትን ሶስት ዓመታት በፔትሮጄት ክለብ ውስጥ በአምበልነት ቡድኑን እየመራ ወሳኝ የሚባሉ ግቦችን ለክለቡ ሲያስቆጥርም ቆይቷል። 

ስኬታማ ዓመታትን በፔትሮጀክት ያሳለፈው ኢትዮጵያዊው የመሀል ሜዳ ተጫዋች ሽመልስ ቀሪ የሶስት ወር ኮንትራት ከፔትሮጀክት ጋር ቢቀረውም በስምምነት  ወደ ሌላኛው የግብፅ ክለብ ምስር ኤልማቃሳ በሶስት ዓመት ውል በይፋ ትላንት ተቀላቅሏል፡፡ ተጫዋቹ የተሳካ የውድድር ዓመት ከአዲሱ ክለቡ ጋር ለማሳካት እንደሚጥርም ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል፡፡

የሽመልሱ አዲሱ ክለብ ምስር ኤልማቃሳ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት መከላከያን በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ መግጠሙ ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *