የአሰልጣኞች አስተያየት | አዳማ ከተማ 1-0 ወልዋሎ ዓ/ዩ

አዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ ዛሬ በአዳማ ከተማ እና ወልዋሎ ዓ /ዩ የተደረገው ጨዋታ በባለሜዳዎቸ 1-0 አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ የቡድኖቹ አሰልጣኞች ተከታዮቹን አስተያየቶች ሰጥተዋል።

” ደረጃ ውስጥ የሚከተን በመሆኑ ውጤቱን በጣም ፈልገነው ነበር ” ሲሳይ አብርሀም – አዳማ ከተማ

ስለጨዋታው

” ባለፈው ጨዋታ ብዙ ኳሶች ስተን ነጥብ የጣልንበት በመሆኑ ዛሬ ተጫዋቾቼ ላይ በአዕምሮ ረገድ ጫና ነበር። በዛ ላይ የዛሬው ጨዋታ ደረጃ ውስጥ የሚከተን በመሆኑ ውጤቱን በጣም ፈልገነው ነበር። በመሆኑም ግብ ካስቆጠርንም በኋላ ተጫዋቾቼ ወደ ኋላ አፈግፍገው ነበር። ያም ውጤቱን ለማስጠበቅ ከነበረራቸው ፍላጎት ነው እንጂ ወደ ፊት ገፍተው እንዲጫወቱ ነግሪያቸው ነበር። ደረጃችንን በማሻሻላችንም ግን በጣም ደስ ብሎናል።”

ስለ ቡልቻ ሹራ የሜዳ ላይ ባህሪ

” የሚገርመው ከጨዋታው በፊት ወጣቶችም ስለሆኑ በረከት እና እሱን እንዲጠነቀቁ ነግሪያቸው ነበር። በግልም ቡልቻን ብዙ ጊዜ ነግሬዋለው። ግን ያው ሜዳ ላይ ስሜታዊ ይሆናል። መውጣቱ ቡድኑንም በጣም የሚጎዳው ነው። በሂደት እየተነጋገርን የምናስተካክለው ይሆናል። ”

” ከሜዳችን ውጪ እንደመጫወታችን ውጤቱ ብዙ አስከፊ አልነበረም። “ፀጋዬ ኪዳነማርያም – ወልዋሎ ዓ /ዩ

ስለጨዋታው

” ጨዋታው ጥሩ ነበር ፤ በሁለታችንም በኩል ጥሩ ፉክክር የታየበት ነበር። የገባብንም ኳስ ዕረፍት ልንወጣ ስንል ከትኩረት ማጣት የተነሳ ነበር። ከዛ ውጪ በሁለታችንም በኩል ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ ነበር። በዚህ ወጤት መጠናቀቅ ያነበረበት ባይሆንም ውጤቱን ተቀብለን በቀጣይ አርመን እንቀርባለን። ”

በተጨዋቾች አጠቃቀም ዙሪያ

” ዛሬ ኦዶንጎ ጉዳት ላይ የነበረ በመሆኑ ያለተፈጥሮ አጥቂ ነበር የተጫወትነው። ያው ዋለልኝም ጉዳት ላይ እንደሆነ ይታወቃል። በመሆኑ በአጫጭር አጥቂዎች እና በመስመር ነበር ለመጠቀም የሞከርነው። ሆኖም ከሜዳችን ውጪ እንደመጫወታችን ውጤቱ ብዙ አስከፊ አልነበረም። “

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *