የአሰልጣኞች አስተያየት | ጅማ አባ ጅፋር 2-0 ወላይታ ድቻ

ጅማ አባጅፋር ወላይታ ዲቻን አስተናግዶ 2-0 ካሸነፈበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተውናል።

” ከዚህ በኋላ ሙሉ ትኩረታችን ፕሪምየር ሊጉ ላይ ይሆናል ” ዩሱፍ ዓሊ – ጅማ አባጅፋር


ስለጨዋታው

” ጨዋታው ጥሩ ነበር። ኳስ ተቆጣጥረን ለመጫወት ሞክረን ነበር። ሆኖም ሜዳው አላጫውት ስላለን በረጃጅም ኳሶች ለመጠቀም ተገደናል። በይበልጥ እየተዘጋጀን የምንገኘው ለእሁዱ (ከኢትዮጵያ ቡና) እና ከዛ በኋላ ለሚጠብቁን የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ነው። ለዛም ነው መስዑድን ሙሉ ጨዋታ ያላጫወትነው።” ” ያገኘናቸውን አጋጣሚዎች አለመጠቀማችን ዋጋ አስከፍሎናል” አሰልጣኝ ዘነበ ፍሰሀ – ወላይታ ድቻ


ስለ ጨዋታው

” ተመጣጣኝ ጨዋታ ነበር። ያገኘነውን አጋጣሚ አለመጠቀምና የተከላካይ ክፍሉ መዘናጋት ዋጋ አስከፍሎናል። ምናልባት ያገኘናቸውን አጋጣሚዎች ወደ ግብ ቀይረን ቢሆን ኖሮ ውጤቱ ይሄ ላይሆን ይችል ነበር። በተቃራኒው ጅማዎች ያገኙትን አጋጣሚ በማስቆጠራቸው ልንሸነፍ ችለናል። ”


ከደጋፊዎች ስላለባቸው ጫና 

ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን ከሜዳችን ውጭ እንደመጫወታችን ሽንፈቱ ጫና ሊፈጥርብን ይችላል። ሁልጊዜ ወደ ሜዳ ስንገባ ለማሸነፍ ነው። ሜዳ ላይ ደግሞ የተለየ ውጤት ሊገጥም ይችላል። በቀጣይ በሜዳችን የምናደርገውን ጨዋታ አሸንፈን ወደ ድል እንመለሳለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *