ብሄራዊ ቡድኑ ለኮንጎው ጨዋታ ዝግጅት ጀምሯል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ህዳር 4 እና 7 ቀን 2008 ከሪፑብሊክ ኦፍ ኮንጎ ጋር ለሚያደርገው የዓለም ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታ የሚረዳውን ዝግጅት ዛሬ ጀምሯል፡፡ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ለ23 ተጫዋቾች ከቀናት በፊት ጥሪ በማድረግ ዛሬ ረፋድ ልምምድ የጀመሩ ሲሆን 20 ተጫዋቾችም ልምምድ ሰርተዋል፡፡

በዛሬ ልምምድ ላይ ያልተገኙት አስቻለው ታመነ ፣ በረከት ይስሃቅ እና አስቻለው ግርማ ናቸው፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አስቻለው ታመነ በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታ አዳማ ላይ መጠነኛ ጉዳት ያጋጠመው በመሆኑ በዛሬው ልምምድ ላይ ያልተገኘ ሲሆን ነገ ልምምድ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሀዋሳ ከነማዎቹ በረከት ይስሃቅ እና አስቻለው ግርማ ደግሞ ከድሬዳዋ ጨዋታ መልስ አዲስ አበባ ለመድረስ በመዘግየታቸው ምክያት የዛሬው ልምምድ ላይ መካፈል ባይችሉም ዛሬ ሆቴል ገብተው ነገ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዛሬው ልምምድ ላይ በግማሽ ሜዳ ፈጣን ቅብብሎችን እና በጠባብ ቦታ መቀባበልን ሲለማመዱ ተስተውሏል፡፡

ዋልያዎቹ ከ9 ቀናት በኋላ የመጀመርያ ጨዋታቸውን በአዲስ አበባ ስታድየም ሲያደርጉ የመልሱ ጨዋታ ከ3 ቀን በኋላ በብራዛቪል ይካሄዳል፡፡ ከወሳኙ ማጣርያ በፊትም የአቋም መለኪያ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

በዚህ ምርጫ በብሄራዊ ቡድኑ ከተካተቱት መካከል - ታከለ ፣ ይሁን እና ያሬድ
በዚህ ምርጫ በብሄራዊ ቡድኑ ከተካተቱት መካከል – ታከለ ፣ ይሁን እና ያሬድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *