ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ | ኢትዮጵያ ቡና መከላከያን አሸንፏል

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ አራሀኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ በተለያዩ የአዲስ አበባ እና የክልል ከተማ ሜዳዎች ሲደረጉ የሳምንቱ ጠንካራ ጨዋታ የነበረው የኢትዮጵያ ቡና እና መከላከያ ጨዋታ በቡና 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ኒያላ ሜዳ ረፋድ 04:00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ኳሱን አደራጅቶ በሚፈለገው መልኩ ለአጥቂዎች ኳሶችን በማድረስ በኩል ከፍተኛ ክፍተት የታየ ሲሆን መከላከያ የመጀመርያዎቹ አስራ አምስት ደቂቃዎች ከኢትዮጵያ ቡና በተሻለ ከተከላካዮች ለመስመር አጥቂያቸው መሐመድ አበራ በተደጋጋሚ በሚጣሉ ኳሶች አማካኝነት የጎል ዕድሎችን ለመፍጠር ጥረት ከማድረግ ውጭ ይህ ነው የሚባል የተሳካ የጎል ሙከራ ሲያደርጉ አልታየም። ኢትዮጵያ ቡናዎች በአንፃሩ ከጨዋታው 25 ደቂቃ በኋላ የተቀዛቅዘ ጅማሬያቸውን አስተካክለው ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታው በመመለስ ማጥቃት የጀመሩ ሲሆን በተለይ 26 ኛው ደቂቃ አጥቂያቸው ገዛኸኝ እንዳለ የመታውን ኳስ ግብጠባቂው ስጦታው አበበ ያዳነበት እንዲሁም በ35 ኛው ደቂቃ ገዛኸኝ እንዳለ ወደ ጎል ሲመታው ግብ ጠባቂው የመለሰውን ኤፍሬም ታደሰ አግኝቶ ተከላካዮች ሲመልሱት እንደገና በየነ ባንጃ አግኝቶ አገባው ሲባል ተከላካዮች እንደምንም ተሸራተው ያወጡባቸው አጋጣሚ ጎል መሆን የሚችል የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበር። ጨዋታው ረጃጅም ኳሶች የበዛበት ሆኖ ቀጥሎ 40ኛው ደቂቃ ላይ የመከላከያ የግብ ክልል ውስጥ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት በቡድኑ አምበሉ ፉዓድ ነስሩ ወደ ጎልነት በመቀየር ቡናዎችን መሪ ማድረግ ቻለ።

ከእረፍት መልስ መከላከያዎች ተዳክመው ሲቀርቡ ኢትዮጵያ ቡና በአንፃሩ ጎል በማስቆጠራቸው ተነቃቅተው በመመለስ በተሻለ ጥሩ እንቅስቃሴ ማደረግ ችለዋል። በተለይ ታንዛኒያ ላይ ባለፈው ዓመት በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና በተመራው እና እስከ ፍፃሜ የዋንጫ ጨዋታ ድረስ በአስደማሚ ሁኔታ ግስጋሴ አድርገው በመጨረሻ በዩጋንዳ በአሳዛኝ ሁኔታ ተሸንፎ ከአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውጪ በሆነው የታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ መልካም እንቅስቃሴ በማድረግ እና ጎሎችን ጎልቶ የወጣው በየነ ባንጃ ዘንድሮ ከአፍሮ ጽዮን ኢትዮጵያ ቡናን በመቀላቀል በሁለቱም መስመሮች እየተቀያየረ ለአጥቂዎች የሚያቀብላቸው ኳሱች እንዲሁም እራሱ የሚሞክራቸው ኳሶች በስፍራው ለነበረ የስፖርት ቤተሰብ አድናቆት እንዲቸረው አድርጎታል። ወደ ፊትም ተስፋ የሚጣልበት ተጫዋች መሆኑን ማሳየት ችሏል። 73ኛው ደቂቃ ላይ ከግራ መስመር ወደ ቀኝ ሰብሮ በመግባት በየነ አመቻችቶ የሰጠውን ገዛኸኝ እንዳለ ለኢትዮጵያ ቡና ሁለተኛ ጎል አስቆጥሯል።

ሁለት ጎል ካስተናገዱ በኋላ በቀሩት ደቂቃዎች ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ቢያደርጉም መከላከያዎች አልተሳካላቸውም። በአንፃሩ ኢትዮጵያ ቡናዎች በመልሶ ማጥቃት ሌላ ጎል ማስቆጠር የሚችሉበትን አጋጣሚዎች ሳይጠቀሙ ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና 2 – 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

የዚህ ሳምንት ጨዋታዎች ውጤቶች እና የደረጃ ሰንጠረዥ የሚከተለውን ይመስላል፡-

ምድብ ሀ
ቅዳሜ ጥር 18 ቀን 2011
ወላይታ ድቻ PP
ሶዶ

ሲዳማ ቡና
እሁድ ጥር 19 ቀን 2011
ኢትዮጵያ ቡና 2-0
ኒያላ
መከላከያ
ኢ/ወ/ስ/አካዳሚ 1-1
አካዳሚ
ሀዋሳ ከተማ
አምቦ ጎል 2-3
አምቦ
ድሬዳዋ ከተማ
ማክሰኞ ጥር 21 ቀን 2011
ጥሩነሽ ዲባባ 9:00
አሠላ
ቅዱስ ጊዮርጊስ

[team_standings 43097]


ምድብ ለ
ቅዳሜ ጥር 18 ቀን 2011
አዳማ ከተማ 5-1
አዳማ

ፋሲል ከነማ
አዲስ አበባ ከተማ 2-2
ኒያላ
ኢትዮጵያ መድን
ወልቂጤ ከተማ 2-5
ወልቂጤ
አሰላ ኅብረት
እሁድ ጥር 19 ቀን 2011
ኢትዮ ኤሌክትሪክ 1-1
ኤሌክትሪክ
አፍሮጽዮን ኮ.
 አራፊ ቡድን – ሀላባ ከተማ

[team_standings 43098]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *