የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በመጪው ቅዳሜ ከኮንጎ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዛሬው እለትም ለተመልካች ክፍት በሆነ ጨዋታ እርስ በእርስ ተጫውተዋል፡፡
በልምምድ ግጥሚያው 24 ተጫዋቾች በአረንጓዴ እና ቢጫ ማልያ ለሁለት ተከፍለው የተጫወቱ ሲሆን የሁለቱ ቡድን ተሰላፊዎች የሚከተሉት ነበሩ፡-
አረንጓዴ – ታሪክ ጌትነት (በእረፍት ሰአት በይድነቃቸው ኪዳኔ ተቀይሯል) ፣ ስዩም ተስፋዬ ፣ ሳላዲን በርጊቾ ፣ አንተነህ ተስፋዬ ፣ ዘካርያስ ቱጂ ፣ በኃይሉ ግርማ ፣ አስቻለው ግርማ ፣ ኤልያስ ማሞ ፣ ቢንያም በላይ ፣ ጌታነህ ከበደ ፣ ዳዊት ፍቃዱ
ቢጫ – አቤል ማሞ ፣ አዲሱ ተስፋዬ ፣ ያሬድ ባየህ ፣ አስቻለው ታመነ ፣ ነጂብ ሳኒ ፣ ጋቶች ፓኖም ፣ ሽመልስ በቀለ (በእረፍት ሰአት በይሁን እንደሻው ተቀይሯል) ፣ በረከት ይስሃቅ ፣ ታከለ አለማየሁ ፣ መሃመድ ናስር ፣ ምንይሉ ወንድሙ
በአረንጓዴ ለባሾች 5-0 አሸናፊነት በተጠናቀቀው ጨዋታ ጌታነህ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ዳዊት ሶስት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
ከኮንጎው ጨዋ በፊት የወዳጅነት ጨዋታ ማግኘት ያልቻሉት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በዛሬው የዝግጅት ጨዋታ የተጫዋቾቻቸውን አቋም ይመዛናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዛሬው የዝግጅት ጨዋታ ዋሊድ አታ እና ራምኬ ሎክ አልተካፈሉም፡፡ ትላንት ሌሊት አዲስ አበባ የገባው ዋሊድ አታ ለዛሬው ጨዋታ ያልደረሰ ሲሆን ብሄራዊ ቡድኑንም እስካሁን አልቀላቀለም፡፡ ትላንት በፍርድ ቤት ጉዳይ ልምምድ ያልሰራው ራምኬል ሎክ ዛሬም አልተገኘም፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ ነገ ረፋድ ላይ ቀጣይ ልምምዱን ያደርጋል፡፡