የአሰልጣኞች አስታያየት | ጅማ አባ ጅፋር 3-3 ድሬዳዋ ከተማ

በ4ኛው ሳምንት ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታ ጅማ ላይ  ጅማ አባጅፋር ከድሬዳዋ ከተማ 3-3 ከተለያዩ በኃላ የሁለቱ ክለብ አሰልጣኞች አስተያየታቸውን እንደሚከተለው ሰጥተዋል፡፡

” የግብ ጠባቂያችን ክፍተት ተጫዋቾቻችንን ረብሾብናል ” የሱፍ ዓሊ – ጅማ አባጅፋር (ረዳት አሰልጣኝ)

” የግብ ጠባቂው ክፍተት ተጫዋቾቻችንን ረብሾብናል፤ ከጨዋታው ሲስተም እንዲወጡም አድርጓል።

” በየአራት ቀናት ልዩነት ነው እየተጫወትን ያለነው። ከተደጋጋሚ ጉዳትና ድካም ማገገም አልቻልንም። ገና ቀሪ ከአራት ጨዋታዎች ይቀሩናል። ለእነሱ ባለን አቅም ስህተቶቻችን አርመን እንዘጋጃለን።

” በዛሬው ውጤት ደስተኛ ነኝ። ከደጋፊዎች ጫና ነበረብን፤ ከመመራት ተነስተን አቻ መውጣታችን ጥሩ ነው፡፡”

” በትኩረት ማነስ ያገባናቸውን ግቦች ማስጠበቅ አልቻልንም” ስምዖን ዓባይ – ድሬዳዋ ከተማ

” ጨዋታው ሁለት መልክ ነበረው። በመጀመሪያው አጋማሽ ከጨዋታ ብልጫ ጋር ሶስት ጎሎችን አስቆጥረን መምራት ችለን ነበር። ሆኖም በተከላዮች ትኩረት ማነስ ያገባናቸውን ግቦች ማስጠበቅ አልቻልንም። የተቆጠሩብን ግቦች ተመሳሳይ ናቸው፤ የትኩረት ማነስ ዋጋ አስከፍሎናል፡፡

” ከእረፍት መልስ ጅማዎች ከኛ በተሻለ ተጫውተዋል። እኛ ሙሉ ለሙሉ የነበረውን ውጤት ለማስጠበቅ ነው የተጫወትነው። ወደፊት ለመሄድ በመልሶ ማጥቃት መጫወት አሰበን ነው የገባነው፤ ተሳክቶልናል። ”


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *