የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች ወደ ልምምድ ይመለሱ ይሆን?

የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች የሶስት ወራት ክፍያ ስላልተፈፀመላቸው ልምምድ አቁመዋል፡፡

የፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮኑ ጅማ አባጅፋር ዘንድሮ በአፍሪካ መድረክ ተሳትፎ ምክንያት ከድካምና ከጉዳት ጋር እየታገሉ እንደ መጀመሪያው ዓመት የፕሪምየር ሊግ ተሳትፏቸው ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ተስኗቸዋል። በተጨማሪም ቡድኑ በፋይናንስ ችግር ምክንያት ላለፉት ሶስት ወራት የተጫዋቾቹን ደምወዝ ባለመከፈሉ በተጫዋቾች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን አስከትሏል። በ4ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ካደረጉት ጨዋታ ቀደም ብለው ልምምድ ለመስራት ፈቃደኝነት አለማሳደራቸው ሲነገር በአዲስ አዳጊው ደቡብ ፖሊስ ከባድ ሽንፈት ማስተናገዳቸውም ለዚህ እንደማሳያ ሊወሰድ ይችላል፡፡

ከደሞዝ ጉዳዮች በተጨማሪ አምና ቡድኑን ለቆ ወደ ግብፅ አቅንቶ የነበረው ኦኪኪ አፎላቢ በአንፃሩ ከሌሎች የቡድኑ ተጫዋቾች ከፍተኛ ደምወዝ ተከፋይ መሆኑና ቅድሚያ የአራት ወራት ደሞዝ መቀበሉ በቡድኑ ተጫዋቾች መካከል ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሮ ቆይቷል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያ እንዳገኘችሁ መረጃ ከሆነም ከደቡብ ፖሊስ ጨዋታ መልስ ልምምድ መስራት ማቆማቸውና ያልተከፈላቸው የሶስት ወር ደምወዝ እንዲከፈላቸው ጥያቄ አቅርበው ዛሬ ጠዋት ከቡድኑ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ደመወዛቸው እንደሚከፈላቸው ቃል የተገባላቸው ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ በ6ኛ ሳምንት ከደደቢት ጋር ለሚጠብቃቸው ጨዋታ እንዲዘጋጁ በመስማማት ተለያይዋል፡፡ ትላንት ልምምድ ሳይሰሩ የቀሩት ተጫዋቾችም ዛሬ አመሻሽ ክፍያው ካልተፈፀመላቸው ልምምድ እንደማይጀምሩ ተሰምቷል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *