ድሬዳዋ ከተማ ለስድስት ተጫዋቾች ማስጠንቀቂያ ሰጠ

ድሬዳዋ ከተማ ለስድስት የክለቡ ተጫዋቾች የማጠንቀቂያ ደብዳቤ መስጠቱን አስታውቋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለክለቡ ጥቂት ጨዋታዎች ላይ ብቻ የተሰለፉ እንዲሁም በተፈለገው ልክ የተሰጣቸውን ዕድል በአግባቡ መጠቀም አልቻሉም በሚል ለአማረ በቀለ፣ ዮናታን ከበደ፣ ኃይሌ እሸቱ፣ ወሰኑ ማዜ፣ ቢኒያም ጥዑመልሳን እና ጋናዊው ሲላ መሐመድ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤው ደርሷቸዋል። 

ድሬዳዋ በሁለተኛው ዙር የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከደረሳቸው መካከል እስከ አራት ተጫዋቾች ሊቀንስ እንደሚችል እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማምጣት ማሰቡን ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ይጠቀማል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *