የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች ወደ ልምምድ ተመልሰዋል

የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋቾች ያለፉት ሦስት ወራት ደሞዛቸው ባለመከፈሉ ምክንያት የደቡብ ፖሊስ ጨዋታን አድርገው ወደ ጅማ ከተመለሱ በኋላ ልምምድ አቁመው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ጠዋት ከቡድኑ አመራሮች ጋር በተደረገው ውይይት ዛሬውኑ እንደሚከፈላቸው በተገባላቸው ቃል መሰረት ደሞዛቸው ዛሬ ከሰዓት ወደአካውታቸው መግባቱን የከተማው ወጣቶችና ስፖርት ኃላፊ እንዲሁም የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አጃኢብ አባመጫ ለሶከር ኢትየኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ዛሬ ማምሻውን በተደረገው ልምምድ በግል ጉዳይ ወደ ኔዘርላንድ አቅንቶ የነበረው ግብ ጠባቂው ዳንኤል አጄይን ጨምሮ ከአጠቃላይ ሰላሳ ተጫዋቾች መካከል አስራ ስምንቱ ተገኝተው ልምምዳቸውን መስራታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ በቦታው በመገኘት ተመልክታለች።

በዛሬው የልምምድ መርሐ ግብር ከዚህ ቀደም በደቡብ ፖሊሱ ጨዋታ ላይ ልምምድ ሳይሰራ ወደ መጀመርያ አሰላለፍ የተካተተው የመሀል ተከላካዩ አዳም ሲሶኮን ጨምሮ ማማዱ ሲዴቤ እና ዲዲዬ ለብሪ ልምምድ ካልሰሩ ተጫዋቾች መካከል ይገኙበታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *