ወላይታ ድቻ አንድ ተጫዋች አሰናበተ

በወላይታ ድቻ አንድም ጨዋታን ማድረግ ያልቻለው የግራ መስመር ተከላካዩ ታረቀኝ ጥበቡ ከክለቡ ጋር ተለያይቷል፡፡

ከሀድያ ወደ ቀድሞ ክለቡ ከአምስት ዓመታት በኃላ መመለስ የቻለው የግራ መስመር ተከላካዩ ታረቀኝ ጥበቡ ለቡድኑ በየትኛውም ጨዋታ ላይ መሠለፍ ያልቻለ ሲሆን ግማሽ የውድድር ዓመትን ካሳለፈ በኃላ ተሰናብቷል። ክለቡ ከተጫዋቹ ስንብት ሌላ በርከት ላሉ ተጫዋቾች ከአቋምና ከዲሲፕሊን ችግሮች ጋር በተያያዘ ማስጠንቀቂያም ሰጥቷል፡፡

በቅርቡ ከአሰልጣኝ ዘነበ ፍሰሀ ጋር በስምምነት የተለያየው ወላይታ ድቻ በ15ኛ ሳምንት በጊዜያዊ አሰልጣኙ ደለለኝ ደቻሳ እየመራ ቅዱስ ጊዮርጊስን የረታ ሲሆን በዚህ ሳምንት ውስጥ አዲስ አሰልጣኝ ወደ ክለቡ እንደሚያመጣ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *