ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኙን አሰናበተ

ኢትዮጵያ ቡና ፈረንሳያዊው የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜስን በዛሬው ዕለት ማሰናበቱ ተረጋግጧል።

ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አሰልጣኝ ጎሜስ ጥሩ በዘንድሮው የውድድር ዓመት መልካም ጅማሮ ቢያደርጉም ቀስ በቀስ ውጤት እየራቃቸው መምጣቱ እና በሜዳ ላይ ቡድኑ የሚያሳየው አሳማኝ ያልሆነ እንቅስቃሴ ማድረጉ ከደጋፊ ተቃውሞ እንዲቀርብ አድርጎታል።

ከሳምንታት ወዲህ አሰልጣኙ ከክለቡ ጋር ሊለያዩ እንደሚችሉ ሲጠበቅ የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት ረፋድ ቡድኑን ልምምድ ካሰሩ በኋላ የቦርዱ የስንብት ውሳኔ እንደደረሳቸው ለማወቅ ተችሏል።

እስከ 2021 ድረስ የሚያቆይ ኮንትራት ከወራት በፊት መፈረማቸው የሚታወሰው ጎሜስ የውል ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን ክለቡ ይፋ ሲያደርግ የምናሳውቅ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *