ስሑል ሽረዎች አንድ ተጫዋች ሲያስፈርሙ ከሁለት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ተለያይተዋል

በሁለተኛው ዙር ተጠናክረው ለመቅረብ ተጫዋቾችን በማሰናበት እና አዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም የተጠመዱት ስሑል ሽረዎች ያስር ሙገርዋን ሲያስፈርሙ ከሚድ ፎፋና እና ስለሞን ገብረመድኅን ጋር በስምምነት ተለያይተዋል።

ዩጋንዳዊው የቀድሞ የኦርላንዶ ፓይሬትስ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ ተጫዋች በ2016 የደቡብ አፍሪካው ታላቅ ክለብ ኦርላንዶ ፓይሬትስ ለቆ ወደ ፈረሰኞቹ ከተቀላቀለ በኋላ ከቡድኑ ጋር አንድ የውድድር ዓመት አሳልፎ ነበር ወደ ፋሲል ከነማ ያቀናው። ተጫዋቹ አምና በርካታ ጨዋታ ላይ ተሳትፎ ቢያደርግም ዘንድሮ ግን ከመጀመርያ አሰላለፍ ውጪ ሲሆን መቆየቱን ተከትሎ የመልቀቂያ ጥያቄ አቅርቦ በስምምነት በመለያየቱ ወደ ሽረ አምርቷል።

በሁለተኛው ዙር በሳምሶን አየለ አሰልጣኝነት ለመመራት ቅጥር የፈፀመው ሽረ ከሙገርዋ ቀደም ብሎ ባሳለፍነው ሳምንት አሳሪ አልመሐዲን ማስፈረሙ ይታወሳል።

በከርካታ ተጫዋቾችን እያሰናበተ የሚገኘው ሽረ ዛሬም ከሁለት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ተለያይቷል። በክረምቱ ክለቡን የተቀላቀሉት ሰለሞን ገብረመድኅን እና አይቮሪኮስታዊው አጥቂ ሚድ ፎፎና ቡድኑን የለቀቁ ተጫዋቾች ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *