እድሉ ደረጄ ወደ ባርሴሎና ሊጓዝ ነው

አሰልጣኝ እድሉ ደረጄ ለአንድ ወር የሚቆይ የእግርኳስ አሰልጣኞች ትምህርት ለመውሰድ ወደ ስፔን ባርሴሎና ያቀናል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በተለያዩ ክለቦች በተጫዋችነት አሳልፎ በኢትዮጵያ ቡና ተስፋ እና ዋናው ቡድን የአሰልጣኝነት ህይወቱን የጀመረው፤ ቀጥሎም በሰሜን ሸዋ ደብረብርሀን ያሰለጠነው እድሉ ደረጄ በስፔኗ ባርሴሎና የአሰልጣኞች ትምህርት ከሚሰጠው mbp ከተሰኘ የትምህርት ተቋም ጋር ባደረገው ግኑኝነት ነው ለአንድ ወር የሚቆየውን የትምህርት ለመከታተል ወደ ስፍራው የሚያቀናው።

ከ20 ቀን በኋላ ወደ ባርሴሎና የሚሄደው እድሉ ኢትዮጵያ ከሚገኘው ስፔን ኤምባሲ ለቪዛ የሚሆነውን ቅድመ ክፍያ 500 ዮሮ ከራሱ ወጪ በማድረግ ከፍሏል። ይሁን እንጂ ለትምህርት፣ ለትራንስፖርት እና ለሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች ከ3000 ሺህ ዩሮ በላይ ያስፈልገዋል። ሆኖም ይህን ብር ለመክፈል የአቅም ውስንነት ያጋጠመው በመሆኑ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ድጋፍ እንዲያደርግለት በደብዳቤ ጥያቄውን እንዳቀረበ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፃል።

የቀድሞ ተጫዋች እና የአሁኑ አሰልጣኝ እድሉ ደረጄ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስፖርት ሳይንስ የመጀመርያ ድግሪ ያለው ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በስፖርት ማኔጅመት ሁለተኛ ዲግሪውን እየሰራ ይገኛል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *