ጅማ አባጅፋር ከሁለት ተጫዋቾች ጋር ተለያየ

ጅማ አባ ጅፋር የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቾቹ ብሩክ ገብረዓብ እና ቢስማርክ አፒያ ጋር ተለያይቷል።

በክረምቱ ጅማ አባጅር ከተቀላቀሉ የውጭ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ጋናዊው ኢንተርናሽናል ቢስማክ አፒያ በአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ላይ መልካም አጀማመር ቢያደርግም በፕሪምየር ሊጉ እንደተጠበቀው መቀሳቀስ አልቻለም። የኦኪኪ አፎላቢ ዳግም ወደ ጅማ አባጅፋር መቀላቀልን ተከትሎም በቡድኑ ውስጥ የሚገኙ የውጭ ተጫዋቾች ቁጥር ስድስት በመድረሱ ኮታውን ለኦኪኪ ለቋል።

ሌላኛው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ብሩክ ገብረዓብ ከስሑል ሽረ ክለቡን የተቀላቀለው በክረምቱ የዝውውር ወቅት ሲሆን በጅማ አባጅፋር በቂ የመሰለፍ እድልን አለማግኘቱን ተከትሎ ክለቡን ለቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *