ከጅማ ጋር የለቀቁት ሁለት ተጫዋቾች ወደ ስሑል ሽረ አመሩ

ስሑል ሽረዎች ትላንት ከጅማ አባ ጅፋር ጋር በይፋ የተለያዩት ሁለት የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቾችን ዝውውር በማጠናቀቅ የግላቸው አድርገዋል፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ስሑል ሽረ ከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያድግ ጉልህ ሚና ከነበራቸው ተጫዋቾች አንዱ የነበረው ብሩክ ገብረዓብ በክረምቱ ወደ ጅማ አባ ጅፋር ቢያመራም የመሰለፍ እድል ባለማግኘቱ በስምምነት በመለያየት ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል።

ሌላው ክለቡን የተቀላቀለው ጋናዊው የፊት መስመር አጥቂ ቢስማርክ አፒያ ነው። በክረምቱ በሁለት ሳምንት ሙከራ ጅማ አባጅፋርን ከተቀላቀለ በኋላ ጥሩ አጀማመር ቢያደርግም ጉዳት ካጋጠመው በኋላ ወደ መጀመርያ አሰላለፍ ለመካተት ተቸግሮ ቆይቷል። በተጨማሪም ኦኪኪ አ አፎላቢ ስድስተኛ ተጫዋች ሆኖ ለክለቡ በመፈረሙ ምክንያት የውጪ ተጫዋቾች ኮታን ለማስተካከል ክለቡን ለቆ ወደ ሌላኛው የኢትዮጵያ ክለብ ስሑል ሽረ አምርቷል።

ከበርካታ ተጫዋቾች ጋር የተለያየው ስሑል ሽረ እስካሁን አራት ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ሲቀላቅል ተጨማሪ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *