የመቐለ 70 እንደርታ የቡድን አባላት ለምግባረ ሰናይ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

በዚህ ዓመት መጀመርያ ከፍሬምናጦስ የአረጋዊያን እና አዕምሮ ህሙማን ማዕከል ጋር በአጋርነት በመስራት ላይ የሚገኙት ምዓም አናብስት ዛሬ ማዕከሉን በመጎብኘት የገንዘብ ድጋፍም አድርገዋል። የቡድኑ ተጫዋቾችን ባካተተው ጉብኝት የተቋሙን ስራዎች ተዘዋውሮ በማየት ከድርጅቱ የበላይ ሃላፊዎች በተለያዩ ጉዳዮች ውይይት አድርገዋል።

የምግር ሰናይ ድርጅቱ ስራዎች የሚያስመለክት ዘገቢ ፊልም ጨምሮ በርካታ ገለፃዎችን ባጠቃለለው ጉብኝት የቡድኑ ተጫዋቾች እና የአሰልጣኞች አባላት የ55 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። በተዘጋጀው መድረክ ተገኝተው አስተያያታቸው የሰጡት ዋና አሰልጣኙ ገብረመድኅን ኃይሌ በድጋፉ ደስተኛ መሆናቸው ገልፀው የክለባቸው መንገድ ተከትለው ሌሎች ቡድኖችም መሰል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠቁመዋል። “ምን እንደምል አላቅም ፤ ይህ ለኛ ትልቅ ትምህርት ነው። ሁለት ስሜት ተሰምቶኛል፤ በአንድ በኩል ያሳዝናል በሌላ በኩል ደሞ በጣም ደስ ይላል። ተረጂዎቹ ከመሬት ተነስተው እንደተመለከትነው ጥሩ ደረጃ መድረሳቸው አይቼ በጣም ደስ ብሎኛል። ሌሎች ቡድኖችም የኛን መንገድ ተከትለው መሰል ድጋፎች ላይ ይሳተፋሉ ብዬ አስባለው።” ብለዋል”

ቡድኑ እና የቡድኑ ደጋፊዎች እያደረጉት ባሉት ድጋፍ ያመሰገኑት አባ ገብረመድህን በርኸ ቡድኑ ድርጅቱን በመደገፍ እና በማስተዋወቅ እያደረገው ባለው ነገር አመስግነዋል።

ደጋፊዎች በፍቃዳቸው ከሚያደርጉት በርካታ የበጎ ፍቃድ ተግባራት በተጨማሪ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ፋሲል ከነማ የመሳሰሉ ክለቦች ደጋፊዎቻቸውን በማስተባበር ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ተስተውሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *