ፋሲል ከነማ ከአጥቂው ጋር ተለያየ

በክረምቱ ፋሲል ከነማን ከተቀላቀሉ የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾች መካከል የሆነው ናይጄሪያዊው አጥቂ ኢዴ ኢፌኒ ቤንጃሚን ከክለቡ ጋር ተለያይቷል፡፡

በክረምቱ ከሙከራ ጊዜያት በኋላ አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በማሳመን ቡድኑን ተቀላቅሎ የነበረው ኢዴ በፕሪምየር ሊጉ ስኬታማ ያልሆነ የውድድር ጊዜ አሳልፏል። ከአንድ ጨዋታ በቀር በሁሉም የአንደኛ ዙር ጨዋታዎች ላይ (8 ተቀይሮ በመግባት እና 6 በመጀመርያ ተሰላፊነት) የተጫወተ ቢሆንም ሜዳ ላይ በቆየባቸው 646 ደቂቃዎች አንድ ጎል ብቻ አስቆጥሯል። በዚህም ቀሪ የአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ውል እየቀረው በስምምነት ተለያይቷል።

ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃ መሠረት ተጫዋቹ ወደሌላኛው የኢትዮጵያ ክለብ ለማምራት በንግግር ላይ እንደሆነ ሲታወቅ አስቀድሞ ከያስር ሙገርዋ ጋርም የተለያየው ፋሲል ከነማ በቀጣዮቹ ቀናት ከሶስት ተጫዋቾች ጋር ሊለያይ እንደሆነ እና አጥቂ ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ተነግሯል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *