አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ወደ ስዊድን ያመራል

አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለአንድ ወር የሚቆይ የእግር ኳስ አሰልጣኝነት ትምህርት ለመውሰድ ወደ ስዊድን ያቀናል።

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ምሩቅ የሆነው አሰልጣኝ ፍሬው ከደደቢት የሴቶች ቡድን ጋር በ2008 የውድድር ዘመን ስኬታማ ጊዜ በማሳለፍ የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ሲሆን በግሉም ኮከብ አሰልጣኝ ሆኖ በመመረጥ መልካም የአሰልጣኝነት ህይወት ጅማሪ ማድረግ ችሏል። አሰልጣኙ በቀጣይ ሲዳማ ቡና ሴቶች ቡድንን በመያዝ በሦስተኛ ደረጃ ያጠናቀቀ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ በከፍተኛው ሊግ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ እያሰለጠነ ይገኛል።

አሰልጣኙ ስለ የሲዊድኑ የስልጠና አጋጣሚ ስለተፈጠረበት ሁኔታ ሲናገር ” ዕድሉ የተገኘው በሲዳማ በነበረኝ ቆይታ ላይ ነበር። ከሲዊድን ሀገር የጥናት ወረቀት ለመስራት የመጡ ግለሰቦች በወቅቱ ስልጠናዬን እየመጡ ይከታተሉ ነበር። ላርስ ክላሰን የተባለ ስዊድናዊ አንዳንድ ጥያቄዎችን ይጠይቀኝ ነበር ፤ ሁሉንም በቅንንነት ነበር ይመምልሰው። ከሱ ጋር የነበረን ቆይታ ጥሩ የሚባል ነበር። በወቅቱ አብሮት የነበረው ዮሐንስ ወልደሰንበት ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞችንም ሆነ ተጫዋቾችን ለመርዳት ፍላጎት ነበረው። እኔንም ጥሩ ያበራታታኝ ነበር። እንግዲህ ሁሉን ፕሮሰሰ አድርጎ የጨረሰልኝ እሱ ነው። ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረግነው ጨዋታ ባዩት የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ደስተኛ ስለነበሩ በስዊድን የሚደረግ የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ እንደሚጋብዘኝ እና ለስልጠና አስፈላጊውን ነገር እንደሚያሟሉልኝ ገልፀውልኝ ነበር። ከዛም በኋላ በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች እንገናኝ ነበር። ” ብሏል።

አሰልጣኝ ፍሬው በቢሾፍቱ አውቶሙቲቭ ዋና አሰልጣኝነት እየሰራ ቢሆንም የቡድኑ አመራሮች ፍቃድ በማግኘቱ ዛሬ ማምሻውን ወደ ስዊድን ያመራል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *