ወላይታ ድቻ ከተከላካዩ ጋር ተለያይቷል

ወላይታ ድቻ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ካስፈረመው የመሀል ተከላካዩ እርቅይሁን ተስፋዬ ጋር ተለያይቷል፡፡

ስብስቡን ለማጠናከር ትላንት ደጉ ደበበ እና አላዛር ፋሲካን ወደ ቡድኑ የቀላቀለው ወላይታ ድቻ በቡድኑ ውስጥ ብዙም ግልጋሎት እየሰጡ የማይገኙ ተጫዋቾችን እያሰናበተ ይገኛል። ከወር በፊት የቀኝ መስመር ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ታረቀኝ ተስፋዬን ያሰናበተ ሲሆን በድጋሚ ዛሬ ደግሞ ከመሀል ተከላካዩ እርቅይሁን ጋር ተለያይቷል፡፡ በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የአሰልጣኝነት ዘመን 2009 ክረምት ላይ ሀድያ ሆሳዕናን በመልቀቅ የጦና ንቦቹን የተቀላቀላቀለው እርቅይሁን አምና በበርካታ ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ ቢችልም ዘንድሮ በጉዳት ምክንያት እምብዛም የተሰላፊነት ዕድል ማግኘት አልቻለም። በቅርቡም አቋሙን እንዲያሻሽል የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የደረሰው ሲሆን ዛሬ ደግሞ ክለቡ እና ተጫዋቹ ቀሪ የስድስት ወራት ውል እየቀራቸው ሊለያዩ ችለዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *