ድሬዳዋ ከተማ የውሰት ጥያቄ ለጅማ አባ ጅፋር አቀረበ

ድሬዳዋ ከተማ የጅማ አባ ጅፋሩ የመስመር አጥቂን በውሰት ለማስፈረም ለባለቤት ክለቡ በደብዳቤ ጥያቄ አቅርቧል።

ድሬዳዋ ለተከታታይ ሦስተኛ ዓመት በመውረድ ስጋት ውስጥ እየተጫወተ የሚገኝ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ራሱን ከወራጅ ቀጠና በማራቅ በሊጉ የሚኖረውን ቆይታ አስተማማኝ ለማድረግ በዝውውሩ ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል። ሁለቱ አማካዮች ምንያህል ተሾመ እና ኤልያስ ማሞን ያስፈረመው ክለቡ በማጥቃቱ በኩል ያለበትን ችግር ለመቅረፍ የጅማ አባ ጅፋሩ የመስመር አጥቂ ኤርሚያስ ኃይሉን በውሰት እንዲሰጡት ለጅማ አባጅፋር ጠይቋል።

የቀድሞው የኒያላ እና ዳሽን ቢራ ተጫዋች ከፋሲል ከነማ ጋር መልካም የሚባል የውድድር ጊዜ በማሳለፍ ነበር በክረምቱ የዝውውር መስኮት የቀድሞ አሰልጣኙ የሚገኙበት ጅማ አባ ጅፋርን መቀላቀል የቻለው። አባ ጅፋር ወጣ ገባ በሆነ ሁኔታ እየተጫወተ የሚገኘውን ተጫዋች ለድሬዳዋ ይሰጠዋል ወይስ በክለቡ ይቆያል የሚለው በቀጣይ የሚጠበቅ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *