ወላይታ ድቻ የተከላካይ መስመር ተጫዋች አስፈረመ 

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን በዋና አሰልጣኝነት ከሾመ በኃላ ቡድኑን ለማጠናከር አንጋፋውን ተከላካይ ደጉ ደበበ እና አላዛር ፋሲካን ወደ ቡድኑ ማካተት የቻለው ወላይታ ድቻ አንተነህ ጉግሳን ሶስተኛ የክለቡ ፈራሚ በማድረግ በ18 ወራት ውል አስፈርሟል፡፡

2008 ላይ ከዩኒቨርስቲ ከተመረቀ በኃላ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት ከአንደኛ ሊግ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ሊግ ድረስ በሶዶ ከተማ በአምበልት የተጫወተው አነተነህ ከመሐል ተከላካይ በተጨማሪ በመስመር አማካይነት መጫወት ይችላል።

ከዚህ ቀደም በወላይታ ድቻ የተጫወተውና አሁን በፋሲል ከነማ የሚገኘው ሽመክት ጉግሳ ወንድም የሆነው አንተነህ በአዲሱ ክለቡ ከታናሽ ወንድሙና ድንቅ የውድድር ዓመት እያሳለፈ ከሚገኘው ቸርነት ጉግሳ ጋር በአንድ ቡድን የሚገናኝ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *