የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2008 የውድድር ዘመን ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም ተጀምሯል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡናም ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በ9፡00 እቴጌን የገጠመው ቅዱስ ጊዮርጊስ 9-1 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ሊጉን ጀምሯል፡፡ ግብ የማስቆጠር ቅድሚያውን የያዙት እቴጌዎች ሲሆኑ ብዙነሽ ስለሺ በ8ኛው ደቂቃ ያስቆጠረችው ግብ የ2008 የመጀመርያ ግብ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
የቅዱ ጊዮርጊስን የድል ግቦች ከመረብ ያሳረፉት ታምር ጠንክር (15′ 62′ 70′ 90+3) ፣ ሄለን ሰይፉ (17′ 33′ 45′) ፣ ዮዲት ተክሌ (63) እና ቱቱ በላይ (90) ናቸው፡፡
በ11፡00 የተደረገው የኢትዮጵያ ቡና እና ልደታ ጨዋታ ከመጀመርያው የተሻለ እንቅስቃሴ የታየበት ነበር፡፡ ለረጅም ደቂዎች በፉክክር በታጀበው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በጨዋታው 2/3ኛ ክፍለጊዜ ባስቆጠራቸው ግቦች ተጠቅሞ 3-1 ማሸነፍ ችሏል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ማእድን ሳህሉ በ29ኛው ደቂቃ ባስቆጠረችው ግብ መምራት ሲችሉ አዲስ መጪዎቹ ልደታዎች በነፃነት አበበ የ45ኛ ደቂቃ ግብ አቻ መሆን ችለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና 3 ነጥቡን እንዲያሳካ የረዳቸውን ግብ ቤተልሄም ታዬ በ76ኛው ደቂቃ እንዲሁም ማእድን ሳህሉ በ82ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የመካከለኛ ሰሜን ዞን 1ኛ ሳምንት ነገ ሲቀጥል በ9፡00 ቅድሰተ ማርያም ከመከላከያ
በ11፡00 ደደቢት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፋለማሉ፡፡