የአሰልጣኞች አስተያየት | ድሬዳዋ ከተማ 1-0 ኢትዮጵያ ቡና

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና ያደረጉት ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ስምዓን ዓባይ – ድሬዳዋ ከተማ

ስለ ጨዋታው

” ከዚህ ቀደም በሜዳችን በምናደርገቸው ጨዋታዎች ዋጋ እየከፈልን እንወጣ ነበር። ዛሬ ግን ውጤቱን እንደመፈለጋችን በተጫዋቾቼ እና ሜዳ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረጋችን በሦስት ነጥቡ ደስተኛ ነኝ። እነርሱ ኳሱን ይዘው ለመጫወት ጥረት ቢያደርጉም እኛ የሜዳ ክፍል ሲደርሱ በተከላካዮቻችን ጥንካሬ መቆጣጠር ችለናል። አሁንም ቢሆን ከዚህ ቀደም የነበረብንን ያገኘነውን አጋጣሚ ያለመጠቀም ክፍተት አሁንም ስራ ይጠብቀናል።

ከእረፍት መልስ ብልጫ ስለመወሰዱ

ጫና የፈጠረብን የፍፁም ቅጣት ምቱ ከሳትን በኋላ ነው። ያ ደግሞ ስነ ልቦናቸውን አውርዶት ነበር። ይህ ማለት በሜዳችን የነበረን አሸንፎ የመውጣት ችግር እና ውጤቱን አስጠብቀን ለመውጣት ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ የመረበሽ ነገር ታይቶባቸዋል። ይሄም ቢሆን በኢትዮጵያ ቡና በኩል ከባድ ነው የምትለው የጎል ሙከራ ማየት አልተቻለም።

ቡድኑን የተቀላቀሉ አዲስ ፈራሚዎች

ከመጡ ገና አስራ አምስት ቀናቸው ነው። ምንያህል ተሾመ ለእኔ በጣም አስገርሞኛል። ሳመጣውም ይሄን አገልግሎት ከእርሱ ፈልጌ ነው። ሜዳ ውስጥ ይሰራልኝ የነበረው አንደኛ ልምድ አለው፤ ልምዱን ይጠቀማል። ሁለተኛ ታክቲካሊ ዲሲፒሊንድ ነበር። ሦስተኛ ሜዳ ውስጥ ቡድን ይመራል፣ ያደራጃል፣ የግል እንቅስቃሴውም የሚያስከፋ አልነበረም። በቀጣይም ከዚህ የተሻለውን እንደሚያደርግ አስባለው። ኤልያስ ማሞም ወደ ሪትም ሲገባ በጣም ጥሩ እንደሚሆን እና የበለጠ ቡድኑን ከዚህ በተሻለ እንደሚጠቅም እርግጠኛ ነኝ።

ገዛኸኝ ከተማ – ኢትዮጵያ ቡና

ስለ ጨዋታው

ጥሩ መንቀሳቀስ ችለናል። ዛሬ ከትኩረት ማጣት እና ባሉብን ክፍተቶች ምክንያት ውጤቱ አልተሳካም። በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ቡድን ይዘን እንመጣለን።

ጉዳት እና የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቡድኑ ጥሪ የፈጠረው ተፅዕኖ

አዎ ሁለት ተጫዋቾች ብሔራዊ ቡድን ናቸው ያሉት። የተወሰኑ ተጫዋቾች በጉዳት ላይ ናቸው። በዛ ላይ በዛሬው ጨዋታ ላይ ወጣቶችን ተጠቅመናል። ሜዳ ላይ ውጤቱ ጥሩ አይሁን እንጂ ጥሩ ነገር ማሳየት ችለዋል። ከዚህም በኋላ ወጣቶች ላይ እየሰራን እንሄዳለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *