ስሑል ሽረ ሙሉዓለም ረጋሳን አስፈረመ

ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት በዝውውሩ በሰፊው እየተሳተፉ የሚገኙት ስሑል ሽረዎች አንጋፋው አማካይ ሙሉዓለም ረጋሳን አስፈርመዋል።

ለ11 ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫውቶ ከክለቡ ጋር በርካታ ዋንጫዎች ያሸነፈው የቀድሞው የመድን፣ የሃዋሳ ከተማ እና ሰበታ ከተማ አማካይ በዚ ዓመት መጀመርያ ለደቡብ ፖሊስ ፊርማውን አኑሮ ከክለቡ ጋር ዓመቱ ቢጀምርም ባለፈው ወር ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቶ በድጋሚ ወደ ሌላው አዲስ አዳጊ ክለብ ስሑል ሽረ ፊርማውን አኑሯል።

ከፕሪምየር ሊግ ክለቦች በተጨማሪ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለበርካታ ዓመታት ያገለገለው ፈጣሪው አማካይ ከስሑል ሽረ ጋር ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት ነው ለመቆየት የተስማማው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *