የኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት ተስተካካይ ጨዋታ የሚደረግበት ቀን ታውቋል

በኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ባሳለፍነው እሁድ መርሐ ግብር ወጥቶለት የነበረው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አራት ተጫዋቾችን ለብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ በማስመረጡ (ክሪዚስቶም ንታምቢ (ዩጋንዳ)፣ ሐሰን ሻባኒ (ቡሩንዲ)፣ አቡበከር ነስሩ እና አማኑኤል ዮሐንስ (ኦሊምፒክ ቡድን) ምክንያት ባቀረበው የይራዘምልኝ ጥያቄ ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገሩ ይታወሳል።

ይህ ጨዋታ በተስተካካይ መርሐ ግብር የሚካሄድበትን ቀን ፌዴሬሽኑ ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም መሰረት ሐሙስ መጋቢት 26 ቀን 2011 በአዲስ አበባ ስታድየም 11:00 ላይ የሚደረግ ይሆናል።

ከተስተካካዩ ጨዋታ ቀደም ብሎ በ18ኛ ሳምንት ደደቢት መቐለ ላይ በሜዳው ደቡብ ፖሊስን ቅዳሜ ሲያስተናግድ ኢትዮጵያ ቡናም ወደ መቐለ በማምራት ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ይገጥማል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *