ዋለልኝ ገብሬ ጅማ አባጅፋርን ተቀላቅሏል

ጅማ አባ ጅፋር የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዋለልኝ ገብሬን አስፈርሟል።

ዋለልኝ ገብሬ በ2010 ወደ ወልዋሎ ካመራ በኋላ በተለይ በመጀመርያው ዓመት ጥሩ ጊዜ ከቡድኑ ጋር ሲያሳልፍ ዘንድሮ ግማሽ የውድድር ጊዜ ካሳለፈ በኋላ ለመልቀቅ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ከክለቡ ጋር ባሳለፍነው ሳምንት መለያየቱ ይታወሳል።

የቀድሞው የኢትዮ አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ወደ ጅማ በማቅናት በጅማ አባጅፋር የሙከራ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ ለቀጣዮቹ 12 ወራት ለመቆየት በመስማማት ክለቡን የተቀላቀለ ሲሆን በአማካይ ስፍራ ላይ ጥሩ አማራጭ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *