የአዳማ ከተማ ተጫዋቾች ወደ መደበኛ ልምምድ ተመልሰዋል

የአዳማ ከተማ ተጫዋቾች ያለፉትን ሶስት ወራት ደመወዝ ክፍያን ባለማግኘታቸው በትናንትናው ዕለት ልምምድ ማቋረጣቸውን መዘገባችን ይታወቃል።

ከተጫዋች የደሞዝ ክፍያ ጋር ተያይዞ የሚቀርበው ጥያቄ ከሽረ ጨዋታ አስቀድሞ ተከፍሎ እንደሚጠናቀቅ ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ የገለፀ ሲሆን ዛሬ ረፋድ ላይ ቡድኑ በተሟላ ሁኔታ መደበኛ ልምምዱን ሰርቷል። የፊታችን እሁድ ከስሑል ሽረ ጋር በሜዳው ለሚያካሂደው ጨዋታም በጥሩ መንፈስ እየተዘጋጀ መሆኑን ክለቡ ጨምሮ ገልጾልናል።

የውድድር ዓመቱን ሁለተኛ አጋማሽ ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች የጀመረው አዳማ ከአቻ እና ሽንፈት ውጤቶች ለማገገም በ18ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ስሑል ሽረን አዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ እሁድ በ9:00 የሚያስተናግድ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *