ከፍተኛ ሊግ ሐ | ቤንች ማጂ ቡና ስድስት፤ ስልጤ ወራቤ አራት አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈርመዋል

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ ላይ የሚገኙት ቤንች ማጂ ቡና እና ስልጤ ወራቤ በዝውውር መስኮቱ ባደረጉት እንቅስቃሴ በርካታ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል።

ስልጤ ወራቤ አራት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም በምትኩ ደግሞ ከአራት ተጫዋቾች ጋር ተለያይቷል። ከመሐመድ ናስር፣ ተስፋዬ ሰለሞን፣ ሰዒድ ግርማ እና አካሉ አበራ ጋር የተለያየው ወራቤ የቀድሞው አጥቂው መልካሙ ፉንዱሬን ከሀምበሪቾ፣ የቀድሞው የሀድያ ሆሳዕና አጥቂ ተዘራ አቡቴን ከመድን፣ አዮዩት ወንዲፍራውን ከደቡብ ፖሊስ የቀላቀለ ሲሆን በቀጣይ ቀንም አንድ ተከላካይ ለማምጣት ማሰባቸውን አሰልጣኝ አብዱልወኪል አብዱልፈታ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

ቤንች ማጂ ቡና ከ7 ተጫዋቾች ጋር የተለያየ ሲሆን ለነዚህ ምትክ ይሆን ዘንድ ስድስት ተጫዋቾች ሲያስፈርም አንድ ተጫዋቾች ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል። ተዘራ ጌታቸዉ ከለገጣፎ ለገዳዲ (አጥቂ)፣ በላይ አባይነህ ከመድን (አጥቂ)፣ መሐመድ ሁሴን ከቢሾፍቱ አዉቶሞቲቭ (አማካይ)፣ ሚፍታህ ዐወል ከዱከም ከተማ (ተከላካይ) አዳዲስ ፈራሚዎች ሲሆኑ ብሩክ ወንዱ ወደ ዋናው ቡድን ያደገ ነው።

ፎቶ – የቤንች ማጂ ቡና አዳዲስ ፈራሚዎች


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *