ሉሲዎቹ በሞገስ ታደሰ ቤት በመገኘት ድጋፍ አድርገዋል

የፊታችን ረቡዕ በኦሊምፒክ ማጣሪያ ከዩጋንዳ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን የሚያደርጉት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የቡድን አባላት ለሞገስ ታደሰ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ሞገስ በእጁ ላይ የደረሰበት የባጃጅ አደጋ ቀስ በቀስ ስር ሰድዶ የነርቭ ሞተሩን የጎዳ ህመም አጋጥሞት ከቤት መዋል ከጀመረ አስር ወራት መሙላቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በቅርቡ ይህን ተጫዋች ወደ ጤንነቱ ለመመለስ በርካቶች ድጋፍን እያደረጉ ሲሆን ተጫዋቾች ጎደኞቹ እና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችን ጭምር በመሰብሰብ ኮሚቴም ተዋቅሮ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ ዛሬ ማለዳ ደግሞ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች እና የአሰልጣኝ ቡድን አባላትን በሞገስ ታደሰ ቤት ተገኝተው ተጫዋቹን በማፅናናት፤ አልፎም ገንዘብ ሰብስበው ለተጫዋቾቹ ያበረከቱ ሲሆን በተጨማሪነትም  በቀጣይ ከዩጋንዳ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም  በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ የሜዳው ሙሉ ገቢ ለዚሁ ተጫዋች ህክምና እንዲውል ለፌድሬሽኑ ጥያቄንም አቅርበዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *