ወልዋሎ ከአስራት መገርሳ ጋር ሲለያይ አንድ ተጫዋች ወደ ዋና ቡድን አሳደገ

በዓመቱ መጀመርያ ወልዋሎን የተቀላቀለው አስራት መገርሳ በስምምነት ከቡድኑ ጋር ሲለያይ ስምዖን ማሩ ወደ ዋናው ቡድን አድጓል።

አዲስ አሰልጣኝ ከቀጠሩ በኋላ በጥሩ የውጤት መነቃቃት ላይ የሚገኙት ወልዋሎዎች በዚ ዓመት መጀመርያ ከደደቢት ካስፈረሙት ግዙፉ አማካይ አስራት መገርሳ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል።
የእግር ኳስ ህይወቱነሠ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ጀምሮ ለዳሽን ቢራ፣ ደደቢት እና ለኢስራኤሉ ሃፖይል ኒር ራማት ሐሻሮን የተጫወተው አስራት መገርሳ በጉዳት ካልተሰለፈባቸው ጨዋታዎች በስተቀር የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ቀዳሚ ተመራጭ ሆኖ ቡድኑን ማገልገሉ ይታወሳል።

ወደ ዋናው ቡድን ያደገው ተጫዋች የአጥቂ ክፍል ተጫዋቹ ስምዖን ማሩ ነው። ወልዋሎን ለበርካታ ዓመታት በቡድን መሪነት የመራውን እና ባለፈው ዓመት የእድሜ ልክ ቅጣት የተላፈበትን የማሩ ገብረፃድቅ የመጀመርያ ልጅ የሆነው ስምዖን ማሩ ከሽሻይ መዝገቦ፣ በረከት ገእግዚአብሄር እና ሰመረ ካሕሳይ በመቀጠል በዚ ዓመት ወደ ዋናው ቡድን ያደገው አራተኛ ተጫዋች ሆኗል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *