የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ልምምድ ሳይሰራ ቀረ

የኦሊምፒክ ማጣሪያ የመጀመርያ ጨዋታውን ከኢትዮጵያ ጋር ለማድረግ ሌሊት አዲስ አበባ የገቡት የዩጋንዳ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከነገው ጨዋታ በፊት ዛሬ አመሻሽ 11:00 በአዲስ አበባ ስታድየም ሊያደርጉት የነበረው ልምምድ በጣለው ዝናብ ምክንያት ሳይአከናወን ቀርቷል፡፡

የጋንዳ ሴቶች ብሔራዊ ብሔራዊ ቡድን 28 የቡድን አባላትን በመያዝ ኢትዮጵያ ከደረሱ በኋላ ቤስት ዌስተርን ሆቴል ማረፊያቸውን አድርገዋል፡፡ ቡድኑ ዛሬ አመሻሽ 11:00 አዲስ አበባ ስታዲየም በመገኘት ከነገው ጨዋታ በፊት ልምምድ ለመስራት ቡድኑ መገኘት ቢችልም ወደ ሜዳ ከገቡ  በኋላ በጣለው ከባድ ዝናብ ልምምዱን አቋርጠው ለመቀመጥ ተገደዋል፡፡ ቡድኑ ዝናቡ እስኪቆም ጠብቀው ዳግም ወደ ልምምድ ለመግባት ቢያስቡም እየበረታ በመምጣቱ ወደ ሆቴላቸው ተመልሰዋል፡፡


ልምምዱን አቋርጠው በመሄድ ላይ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ቡሌዳ ፋሪዳ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት “ልምምድ አለማድረጋችን የተፈጥሮ ጉዳይ ነው። አለመስራታችን በነገው ጨዋታችን ላይ ተፅዕኖ ቢኖረውም በተቻለን አቅም ውጤት ለማስመዝገብ እንገባለን” ብለዋል።

ከግብፅ የተመደቡት አራቱም ዳኞች ልምምዳቸውን ያከናወኑ ሲሆን ኮሚሽነሯ ከናይጄሪያ አሰሰሩ ደግሞ ከጅቡቲ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *