ቶኪዮ 2020 | ለመልሱ ጨዋታ የሉሲዎቹ የመጀመርያ ተሰላፊዎች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በ2020 የኦሊምፒክ ሴቶች እግርከቀስ ማጣርያ ከዩጋንዳ ጋር የመልስ ጨዋታውን 10:00 ላይ ያደርጋል።

ለጨዋታው የሉሲዎቹ አሰልጣኝ ሠላም ዘርዓይ የመጀመርያ አሰላለፏን ያሳወቀች ሲሆን አዲስ አበባ ላይ ከነበረው አሰላለፍ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ በተከላካይ ስፍራ መሠሉ አበራ (በታሪኳ ደቢሶ) እና ናርዶስ ዘውዴን (በአለምነሽ ገረመው) በአማካይ ስፍራ ደግሞ ህይወት ደንጊሶን (በሰናይት ቦጋለ) አካታለች።

የመጀመርያ አሰላለፍ

ዓባይነሽ ኤርቀሎ

ናርዶስ ዘውዴ – መሰሉ አበራ – መስከረም ካንኮ – ብዙዓየሁ ታደሰ

ብርቱካን ገብረክርስቶስ – ህይወት ደንጊሶ – እመቤት አዲሱ

ሴናፍ ዋቁማ – ሎዛ አበራ – ሰርካዲስ ጉታ

የኢትዮጵያ ካምፓላ ላይ በሚካሄደው በዚህ ጨዋታ ከመጀመርያው የአዲስ አበባ ጨዋታ ያስመዘገበችውን የ3-2 ድል ካስጠበቀች ወደ ተከታዩ የማጣያ ዙር የምታልፍ ይሆናል።