አዳማ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር ተለያየ

ላለፉት ስምንት ወራት አዳማ ከተማን በማሰልጠን የቆዩት አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀ ከቡድኑ ጋር ተለያይተዋል።

የቀድሞው የሼር ኢትዮጵያ እና አክሱም ከተማ አሰልጣኝ ለሁለት ጊዜያት ያህል ከውጤት ጋር እና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ማስተካከል በሚገባቸው ጉዳዮች ዙርያ ደብዳቤ ደርሷቸው የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ በስምምነት ከቡድኑ ጋር መለያየታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በቀጣይ ክለቡን እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በምክትል አሰልጣኝነት ያለፉትን ስድስት ዓመታት ያገለገሉት አስቻለው ኃይለሚካኤል ቡድኑን ተረክበው እንዲያሰለጥኑ ተመድበዋል።

አዳማ ከተማ በመጪው እሁድ በ20 ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሀዋሳ ከተማን ያስተናግዳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡