የ21ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ሐሙስ ይደረጋሉ

በ21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሳይደረጉ የቀሩት ሁለት ጨዋታዎች ሐሙስ እንደሚካሄዱ ተረጋግጧል።

ቅዳሜ ዕለት ሀዋሳ ላይ ሊካሄድ የነበረውና ከጨዋታው በፊት በተከሰተ የፀጥታ ችግር ሳይከናወን የቀረው የደቡብ ፖሊስ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ ሐሙስ ሚያዚያ 17 በአዲስ አበባ ስታድየም እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን 11:00 ጨዋታው የሚደረግበት ሰዓት ነው።

በተመሳሳይ ሀዋሳ ላይ እሁድ ሊደረግ የነበረውና በፀጥታ ስጋት ሳይካሄድ የቀረው የሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታም ሐሙስ ይካሄዳል። ጨዋታው እንዲካሄድባቸው በርካታ ከተሞች በአማራጭነት ተይዘው እንደነበር የተሰማ ሲሆን በመጨረሻ አሰላ ላይ በ09:00 ሰዓት እንዲካሄድ ተወስኗል።

የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ወደ ማክሰኞ ሚያዚያ 22 መሸጋገራቸው ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡