የፕሪምየር ሊጉ 22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ወደ ቀጣይ ሳምንት ተሸጋገሩ

ሀሙስ ሊካሄዱ የነበሩት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሊራዘሙ እንደሚችሉ መዘገባችን ይታወሳል። በዚህም መሰረት ሁሉም ጨዋታዎች ወደ ቀጣይ ሳምንት መሸጋገራቸው ተረጋግጧል።

በተሻሻለው መርሐ ግብር መሰረት ሁሉም የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ማክሰኞ ሚያዚያ 22 ቀን 2011 እንዲካሄዱ ተወስኗል።

መርሐ ግብሩ ይህንን ይመስላል

ጅማ አባ ጅፋር ከ ሲዳማ ቡና (09:00)
ስሑል ሽረ ከ ሀዋሳ ከተማ (09:00)
አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና (09:00)
ባህር ዳር ከተማ ከ ደቡብ ፖሊስ (09:00)
ወላይታ ድቻ ከ መከላከያ (09:00)
ወልዋሎ ዓ/ዩ ከ ደደቢት (09:00)
ፋሲል ከነማ ከ ድሬዳዋ ከተማ (09:00)
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቐለ 70 እንደርታ (11:00)

* በተያያዘ ዜና በ21ኛ ሳምንት ሳይደረጉ የቀሩት ሁለት ጨዋታዎች ሐሙስ ሊካሄዱ እንደሚችሉ ሲገለፅ ትክክለኛ የጨዋታ ቀን እና የውድድሩ ቦታዎች ሲረጋገጡ የምንዘግብ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡