የፕሪምየር ሊጉ 23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መርሐ ግብር ይፋ ሆኗል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መቼ እንደሚደረጉ ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።

በ21ኛ ሳምንት ያልተካሄዱ በተስተካካይ መርሐ ግብር እንዲካሄድ በሚል የሊጉ ጨዋታዎች በአንድ ሳምንት መሸጋሸጋቸው የሚታወስ ሲሆን ሚያዊያ 22 ሊደረጉ የነበሩ የ23ኛ ጨዋታዎችም በተመሳሳይ በአንድ ሳምንት ተገፍቷል።

መርሐ ግብሩ ይህንን ይመስላል፡-

ቅዳሜ ሚያዚያ 26 ቀን 2011
ደቡብ ፖሊስ 09:00 አዳማ ከተማ (ሀዋሳ)
ደደቢት 09:00 ፋሲል ከነማ (መቐለ)
መከላከያ 10:00 ባህር ዳር ከተማ (አዲስ አበባ)

እሁድ ሚያዚያ 27 ቀን 2011
ድሬዳዋ ከተማ 09:00 ወላይታ ድቻ (ድሬዳዋ)
መቐለ 70 እንደርታ 09:00 ስሑል ሸረ (መቐለ)
ሀዋሳ ከተማ 09:00 ሲዳማ ቡና (ሀዋሳ)
ኢትዮጵያ ቡና 10:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ (አዲስ አበባ)

ሰኞ ሚያዚያ 28 ቀን 2011
ወልዋሎ ዓ/ዩ 09:00 ጅማ አባ ጅፋር (መቐለ)

* የዚህ ሳምንት በፊት የሚደረገው የ22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሁሉም ጨዋታዎች ነገ ይደረጋሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡