“እውነት ለመናገር ቡድኔ ያጣው እንደሚካኤል ኦሉንጋ አይነት ተጫዋች ነው፡፡” አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ 

የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ለኬንያዊው አጥቂ ሚካኤል ኦሉንጋ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡ ኡሉንጋ በ2015 የተሳካ የውድድር ዘመን በጎር ማሂያ ያሳለፈ ሲሆን ለክለቡ እና ለሃራምቤ ኮከቦች በሁሉም ውድድሮች 38 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡ 

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ለኬኔያው እግርኳስ ድረገፅ ለሶካ በሰጡት አስተያየት ቡድናቸው እንደኦሉንጋ አይነት አጥቂ ቢይዝ ኖሮ የሴካፋ ሻምፒዮን መሆን ይችል ነበር ብለዋል፡፡

“እውነት ለመናገር ቡድኔ ያጣው እንደሚካኤል ኦሉንጋ አይነት ተጫዋች ነው፡፡ ኦሉንጋ ጥሩ መቺ ነው ፣ ኳስን በግንባሩ ይገጫል፣ ጥሩ አቋም አለው እንዲሁም ኳስ ተቆጣጥሮ መጫወት ይችላል፡፡ ኦሉንጋ በቡድኔ ቢኖር የሴካፋን ዋንጫ በነበሩት ወጣት ተጫዋቾች ማንሳት እችል እንደነበር 1% ጥርጥር የለኝም፡፡” በማለት አሰልጣኝ ዮሃነስ አስገራሚ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

Olunga featured

እንደሶካ ዘገባ ኦሉንጋን የያዘቸው ኬንያ በሴካፋ ዋንጫ ላይ የተለየ ነገር ሳታሳይ መሰናበቷ አስተውሶ ለአሰልጣኝ ዮሃንስ ላቀረበላቸው ጥያቄ ኡሉንጋን በሚገባ ካለመጠቀም ነው ብለዋል፡፡ “የኬንያ አጨዋወት ኡሉንጋን የያዘውን ዕምቅ ችሎታ አውጥቶ እንዳይጫዋት አድርጓታል፡፡ ለምሳሌ በአብዛኛው ግዜ ኡሉንጋ በፊት መስመር ላይ ተሰልፎ በረጃጅም የሚጣሉለትን ኳሶች እንዲሻማ ነው የሚደረገው፡፡ ይህ ደግሞ ለተጫዋቹ ጥሩ አይደለም::”

ሚካኤል ኦሉንጋ የኬንያ ፕሪምየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በመሆን መመረጡ የሚታወስ ነው፡፡ በቅርቡ ስሙ ከሞሮኮው ታላቅ ክለብ ከራጃ ካዛብላንካ ጋር ለዝውውር በስፋት ተያይዞ ተነስቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *