ደደቢት ይግባኝ ጠየቀ

ደደቢቶች በተላለፈባቸው ቅጣት ዙርያ ላይ ለፌደሬሽኑ የይግባኝ ደብዳቤ አስገቡ።

ባሳለፍነው ሳምንት ደደቢት ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው ጨዋታ በደጋፊዎች በኩል በታየው ከስፖርታት ጨዋነት ውጭ የሆነ ተግባር ደደቢት ላይ ቅጣት መተላለፉ ይታወሳል። በቅጣቱ ዙርያ ይግባኝ ይጠይቃሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ሰማያዊዎቹም ከተበየነላቸው ቅጣቶች ሁለቱ ላይ የተገቢነት ጥያቄ አስነስተዋል።

የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደሎችን ተከትሎ የሚመጡትን ቅጣቶች እንደሚቀበሉና እንደሚደግፉ በደብዳብያቸው የገለፁት ደደቢቶች የተላለፈላቸው የገንዘብ ቅጣት እና በዝግ እንዲካሄዱ በተወሰኑት ጨዋታዎች ተገቢ እንዳልሆነ ለፌደሬሽኑ በፃፉት ደብዳቤ አሳውቀዋል።

ደብዳቤው ይህን ይመስላል:-


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡