ስሑል ሽረ ላይ ተጥሎ የነበረው የሜዳ ቅጣት ተነሳ


ባሳለፍነው ወር መጨረሻ በፌደሬሽኑ የገንዘብና የሜዳ ቅጣት የተላለፈባቸው ስሑል ሽረዎች ቅጣታቸው ላይ ማሻሻያ ተደረገ።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ባደረጉት ጨዋታ የቀድሞ የክለቡ ቡድን መሪ በዕለቱ ረዳት ዳኛ ላይ ያልተገባ ባህርይ አሳይተዋል በሚል የ35 ሺህ እና ሁለት የሜዳቸው ጨዋታዎችን ከከተማቸው ውጪ ሁለት መቶ ኪሎሜትር ርቀው እንዲጫወቱ በዲስፕሊን ኮሚቴ የተወሰባቸው አዲስ አዳጊዎቹ የገንዘብ ቅጣታቸው ወደ 5 ሺህ ብር ሲቀነስላቸው ከሜዳቸው ውጭ ወጥተው ሁለት ጨዋታ እንዲጫወቱ የተወሰነባቸው ቅጣትም ሙሉ በሙሉ ተነስቷል።

ቅጣቱ ከተጣለባቸው በኃላ በእግድ እንዲቆይ ይግባኝ ያስገቡት ስሑል ሽረዎች የተቀነሰላቸው ቅጣት ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ እንዲያደርጉ እና ለይግባኝ ያስያዙት ብር ለፌደሬሽኑ ገቢ እንዲሆን ተወስኖላቸዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡