“የእኛ እጣ ፈንታ የሚወሰነው የቡናው ጨዋታ ነው” ገብረመድህን ኃይሌ

ጅማ ላይ ጅማ አባ ጅፋር ከ መቐለ 70 እንደርታ ጋር 2-2 ከተለያዩ በኋላ የመቐለው አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ አስተያየታቸውን ሲሰጡ የጅማው ዩሱፍ ዓሊን አስተያየት ማግኘት አልቻልንም።

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ

ስለዛሬው ጨዋታ

ከዛሬው ጨዋታ ሶስት ነጥቦችን ለማግኘት አስበን ነበር ወደ ሜዳ የገባነው። በመጀመሪያ አስር አስራ አምስት ደቂቃዎች ነገሮች በምንፈልገው መልኩ ነበር የሄዱት። ከሰላሳኛው ደቂቃ በኃላም ጨዋታውን ተቆጣጥረን ጥሩ ነበርን። ከእረፍት መልስ ግን በድንገት በተቆጠሩብን ሁለት ግቦች ተደናግጠን ነበር። ከዛ በኃላ ነው ያንን ተቋቁመን መመለስ የቻልነው። ሁለት ለባዶ ከመመራት ሁለት አቻ መውጣት እንዲሁም ባለቀ ሰዓት ብረት የመለሰብን ጎል ሊሆን የሚችል ነበር። እድለኞች አልነበርንም ፡፡

ስለቀሪ አራት ጨዋታዎች

ደፋ ቀና እያልን የምንገኘው ዋንጫውን ለማንሳት ነው። ጠንካራ ተፎካካሪዎች አሉን። ከፊታችን ከቡና ጋር ነው የምንጫወተው። የእኛ እጣ ፈንታ የሚወሰነው ቡናን ማሸነፍ ስንችል። ነው ከዛ ስንመለስ ጥሩ አድቫንቴጅ ልናገኝ ስለምንችል ለማሸነፍ ማድረግ የምንችለውን እናደርጋለን፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡