ለኢጋድ ከ18 አመት በታች ሴቶች ውድድር 34 ተጫዋቾች ተመርጠዋል

 

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን እድሜያቸው ከ18 አመት በታች በሆኑ ሀገራት መካከል በሚደረገው የኢጋድ (የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት) አባል ሃገራት ውድድር ላይ ትካፈላለች፡፡ በጥር ወር በጅቡቲ አስተናጋጅነት በሚደረገው ውድድር ላይ የሚካፈለው ከ18 አመት በታች ቡድናችን በንግድ ባንኩ አሰልጣኝ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራ ሲሆን ዛሬ 34 ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ተደርጓል፡፡

 

የተመረጡ ተጫዋቾች ዝርዝር

(የተመረጡት ተጫዋቾች እስከ ረቡእ ድረስ ሪፖርት በማድረግ ሀሙስ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ )

ግብ ጠባቂዎች

ትዕግስት አበራ – ሀዋሳ ከነማ

አክሱማዊት ገ/ሚካኤል – ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ

ዋዚት ገበየሁ – ልደታ

ናርዶስ ክንፈ – ሙገር ሲሚንቶ

ሳሳሁልሽ ስዩም – ድሬዳዋ ከነማ

 

ተከላካዮች

ዘለቃ አሰፋ – ደደቢት

መቅደስ ቦራ – ኢትዮጵያ ቡና

አበዛሽ ሞጌሶ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ጥሩወርቅ ወዳጄ – ዳሽን ቢራ

ሰናይት በዳሳ – ቅድስት ማርያም

ሰላም ላእከ – ሙገር ሲሚንቶ

ፅጌ አሳምነው – ኢትዮጵያ ቡና

ቤተልሄም ከፍያለው – ኤሌክትሪክ

ታዩ አረጋ – ልደታ

ዝናቧ ሽፈራው  – ድሬዳዋ ከነማ

 

አማካዮች

ኪፊያ አብዱልራህማን – ደደቢት

ፅዮን ፈየራ – ኤሌክትሪክ

ፅዮን አበራ – ዳሽን ቢራ

ዘይነባ ሰኢድ – ኤሌክትሪክ

ትሁት አየለ – ሲዳማ ቡና

ዮርዳኖስ ፍስሃ – ኤሌክትሪክ

ኤልዛቤጥ ተመስገን – ኢትዮጵያ ቡና

መሪማ ፈትኡ – ቅድስት ማርያም

ሶፋኒት ተፈራ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ዮርዳኖስ አረጋ – ዳሽን ቢራ

ነጻነት ደርቤ – ዳሽን ቢራ

 

አጥቂዎች

ነጻነት መና – ሀዋሳ ከነማ

አስራት አለሙ – ሲዳማ ቡና

ይታገሱ ተ/ወርቅ – ድሬዳዋ

ቤተልሄም ሰማን – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

አለምነሽ ገረመው – ኤሌክትሪክ

ጽዮ ዋቅጅራ – ሀዋሳ ከነማ

እማዋይሽ ይመር – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ሳሳሁ ኃ/ማርያም – ሙገር ሲሚንቶ

 

ኢትዮጵያ ዘንድሮ በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ላይ በተፈጠረ ስህተት መሳተፍ ባትችልም በኢጋድ ከ18 አመት በታች ውድድር እና በ2016 የአለም ከ17 አመትበታች ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ውድድር ላይ ይካፈላል፡፡   igad%20gams%20-%20copy%20-%20copy

ኢጋድ በውስጡ ኢትዮጵያ ፣ ዩጋንዳ ፣ ኬንያ ፣ ኤርትራ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሱዳን ፣ ሶማልያ እና ጅቡቲ በአባልነት ያቀፈ ድርጅት ሲሆን በኤፕሪል 2015 በጅቡቲ በተደረገ የአባል ሃገራት የስፖርት ሚንስትሮች ጉባኤ በኢጋድ ድጋፍ የሚደረግለት የወጣቶች ውድድሮች ለማዘጋጀት ከስምምነት ደርሰው ነበር፡፡ በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያን በመወከል የተገኙትም የህፃናት ፣ ወጣቶች እና ሴቶች ጉዳይ ሚንስትሯ ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ ነበሩ፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *