የሉሲዎቹ አሰልጣኝ ሠላም ዘርዓይ ለወዳጅነት ጨዋታ 25 ተጫዋቾች ጠርታለች

በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች እግርኳስ ማጣርያ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለሁለተኛ ዙር ማጣርያ ዝግጅት ከጋምቢያ ጋር ለሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ 25 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጎላቸዋል።

በሚያዚያ ወር በአንደኛ ዙር ማጣርያ ዩጋንዳን በድምር ውጤት 4-2 አሸንፋ ወደተከታዩ ዙር ያለፈችው ኢትዮጵያ ነሐሴ 26 ከካሜሩን ጋር በሁለተኛ ዙር ማጣርያ የምትጫወት ሲሆን ከወዲሁም ለጨዋታው ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ሰኔ 7 ወደ ጋምቢያ በማምራት ከጋምቢያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ታከናውናለች። ለዚህም እንዲረዳ 25 ተጫዋቾች ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

የ25 ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች፡ ታሪኳ በርገና (ጥረት ኮርፖሬት) ዓባይነሽ ኤርቀሎ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ማርታ በቀለ (መከላከያ)

ተከላካዮች፡ መስከረም ካንኮ (አዳማ ከተማ)፣ ገነሜ ወርቁ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ መሰሉ አበራ (መከላከያ)፣ ቅድስት ዘለቀ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ብዙዓየሁ ታደሰ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ናርዶስ ጌትነት (አዳማ ከተማ)፣ እፀገነት ብዙነህ (አዳማ ከተማ) ነፃነት ፀጋዬ (አዳማ ከተማ)

አማካዮች፡ ህይወት ደንጊሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ እመቤት አዲሱ (መከላከያ)፣ ብርቱካን ገብረክርስቶስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ዓለምነሽ ገረመው (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ሰናይት ቦጋለ (አዳማ ከተማ)፣ አረጋሽ ከልሳ (መከላከያ)፣ ይመችሽ ዘውዴ (ድሬዳዋ ከተማ)

አጥቂዎች፡ ገነት ኃይሉ (አዳማ ከተማ)፣ ምርቃት ፈለቀ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ሎዛ አበራ (አዳማ ከተማ) መዲና ዐወል (መከላከያ)፣ ሴናፍ ዋቁማ (አዳማ ከተማ)፣ ሰርካዲስ ጉታ (አዳማ ከተማ)፣ ሔለን እሸቱ (መከላከያ)

ብሔራዊ ቡድኑ ነገ ተሰባስቦ ዝግጅት ይጀምራል


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ።