ድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኙን በቋሚነት አስቀጥሏል

የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ድሬዳዋ ከተማ ስምዖን ዓባይን በቋሚነት አስፈርሟል።

የውድድር ዓመቱን በዮሐንስ ሳህሌ መሪነት የጀመሩት ብርቱካናማዎቹ ብዙም መዝለቅ ሳይችሉ ከአሰልጣኙ ጋር ከተለያዩ በኋላ ምክትሉ ስምዖን ዓባይ በጊዜያዊነት የመራ ሲሆን ቡድኑ በሁለተኛው ዙር መሻሻል እንዲያሳይ እና ከወራጅነት ስጋት ቀደም ብሎ እንዲላቀቅ ማድረግ ችሏል። ይህም ለቀድሞው የኤሌክትሪክ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ኮተን ኮከብ ቋሚ ውል አስገኝቶለታል። እስከ ቀጣዩ የውድድር ዘመን መጨረሻም በክለቡ የሚቆይ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡